Skip to main content

                የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ወጣት አብዶ ድንቁ መልዕክት 

   የወጣቶች ክንፍ /ቤት ሀላፊ ወጣት አብዶ ድንቁ

               የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት 

 የሀገራችን ወጣቶች ሲያነሱአቸው የነበሩ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተገቢው ትኩረት ተሰጥቶ መፈታት ባለመቻሉ ለውጥ እንዲመጣ መስዋዕትነት በመክፍል የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ወጣቶች የራሳቸውን ድረሻ ተወጥቷል::

የተመዘገቡ ለውጦችን አስጠብቆ ለማስፋት፣ስሕተቶችን ለማረም እና የዛሬውንና የመጪውን ወጣቱ ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የክንፋችን ሚና የማይተካ ነው፡፡ ክንፋችን ሀገራዊ ለዉጡን በመገንዘብ የክልላችን ወጣት በሚመጥን መልኩ እራሱን አደረጅቶ ወደ ስራ በመግባት በስራ እድል ፈጠራ፣በበጎ ፍቃድ ስራ፣ የተጎዱ ወገኖችን ድጋፍ ከማድረግ አንፃር እንዲሁም የፖርቲውን ፅንሳ ሀሳብ በወጣቱ ዘንድ እንዲሰረፅ ከማድረግ አኳያ በረካታ ውጤቶችን አስመዝግበዋል፡፡

አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ሥርዓት ለመዘርጋት የነደፋቸውን ፖሊሲዎች ለወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ውጤታማ እንዲሆን ክንፋችን ከብልጽግና ፓርቲያችን ጎን በመቆም ለውጤታማነቱ ትግል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ፣ክንፋችን የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፤ የግለሰብና ቡድን መብቶች በሚዛኑ የሚከበሩባት፤ የበለጸገች፣ ኅብረብሔራዊ ማንነቷ የዳበረና አንድነቷ የተጠናከረ ኢትዮጵያን በቁርጠኝነት ዕዉን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፣ ወጣቱ ትውልድ በመደመር አስተሳሰብና በአንድነት ቅኝት በመነሣት፣ልናያት የምንፈልጋትን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እና ለወጣቶቿ ምቹ የሆነች ሀገር መገንባት ክንፋችን የራሱን ድርሻ ይወጣል፡፡

 

                                                                                                                                                               የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ወጣት አብዶ ድንቁ 

                                                                                                                   አመሰግናለው!