| ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ! ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለዘንድሮዉ የገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ ! አደረሰን! እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ። ሀገራችን ኢትዮጵያ በታላላቅ ሀገራዊ ስኬቶች ታጅባ፣ የማንሰራራት ዘመን ጉዞዋን እያጠናከረች በምትገኝበት ምዕራፍ ላይ የምናከብረዉ የዘንድሮዉ የገና በዓል ፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴቶቻችንን በማጠናከር ፣በመደመር እሳቤ ተሳስረን፣ ለአዳዲስ ሀገራዊ ብስራቶች ፣በጋራ ለመትጋት መነሳሳትን የምንፈጥርበት ነዉ። የገና በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነዉ። የገና በዓል ከሃይማኖታዊ ትዉፊቶቹ እና አስተምህሮቶቹ ባሻገር ፣ የመልካም ምኞት መግለጫ ስጦታዎችን በመለዋወጥ ፣ ፍቅርንና ትብብርን ለማደስ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነዉ። በዓሉ ማህበራዊ እሴቶችን የሚያነቃቃ፣ የወንድማማችነት/የእህትማማችነት መንፈስን የሚያድስና በአዲስ መንፈስ ለአዲስ ስኬት መነሳሳትን የሚያጎናጽፍ ነዉ። በዓሉን ስናከብር ብሩህ ተስፋንና አሻጋሪ ህልምን ሰንቀን ፣ የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴቶችን አልቀን ፣ ለጋራ ሠላምና ዕድገት በጋራ ለመትጋት ዝግጁነታችንን ከፍ በማድረግ መሆን ይኖርበታል። መልካም የገና በዓል ! አመሠግናለሁ ! Read More |
| ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለገና በዓልየእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትአስተላለፉ ሆሳዕና ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፡- እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ! ዘንድሮ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የምናከብረው የተነገረው የተስፋ ቃል መድረሱን፣ የለውጥ ብርሃን መፈንጠቅ መጀመሩን፣ የመሻገር ዘመን መቅረቡን እያመንን ነው። ጉዟችን በውጣ ውረድ የተሞላ ነበር፤ ተስፋ አስቆራጭ መከራዎችን አስተናግደናል። ከእንግዲህ ፈተናው ጨርሶ አይጎበኘንም ባንልም፣ ተስፋችን የሚወለድበት የዋዜማው ዕለት ላይ ደርሰናል። የፍዳው ዘመን ላይመለስ ተሸኝቶ፣ የማንሠራራት ዘመን እንደመጣ በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን። የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ትናንትን የዋጀ፣ ነገን የታደገ ነው። ከአዳም እስከ ክርስቶስ ልደት የተከናወነው ሁሉ ዋጋ ያገኘው በክርስቶስ መወለድ ምክንያት ነው። ከክርስቶስ ልደት በኋላ ያለው የሰው ልጅ ሕይወት ቀና የሆነው በክርስቶስ ምክንያት ነው። ክርስቶስ በትናንትና በነገ መካከል “ዛሬ” ሆኖ ሁለቱን አስታርቋቸዋል። ለዚህ ነው የክርስቶስን መወለድ በታላቅ ክብር የምናከብረው። ክርስቶስ ባይወለድ ኖሮ ትንቢት የተናገሩ ነብያት፣ መሥዋዕት ያቀረቡ ካህናት፣ ቃል ኪዳን የተቀበሉ አበው፣ ተስፋ ያደረጉ የሰው ልጆች ሁሉ ሥራቸው ታሪክ ብቻ ሆኖ ይቀር ነበር። ዋጋ ከፍሎ ህያው ያደረጋቸው ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ ባይወለድ ኖሮ የሰው ልጅ ወደፊት የሚያከናውናቸው የሥልጣኔ፣ የጽድቅ እና የበጎነት ሥራዎች ሁሉ የድኅነት ቅኝት አይኖራቸውም ነበር። ትናንትን የቀደሰው፤ ነገንም የዋጀው፣ ዛሬ የተወለደው ክርስቶስ ነው። ይሄንን ታላቅ ትምህርት እናስተውል ዘንድ ይገባናል። ትናንት የቱንም ያህል ታላቅ ታሪክ፣ ታላቅ ቅርስ እና ታላቅ ዕሴት ቢኖረንም ዛሬያችን ከተበላሸ ዋጋ የለውም። ባቢሎን እና ፋርስ፣ አቴና እና ሮም፣ ሱሜር እና ሜሶፖታምያ - ዛሬ በጥንቱ ክብራቸውና ታላቅነታቸው የሉም። እነርሱ ትናንት ነበራቸው። ያጡት ዛሬን ነው። ዛሬን በማጣታቸው ደግሞ ትናንታቸው ትዝታ፣ ነጋቸው ሕልም ሆኗል። ትውስታ እንጂ እመርታ የላቸውም። ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ነበረች። የታላላቅ ሥልጣኔዎች ሀገር ነበረች። የታላላቅ መንግሥታትና የታላላቅ ሕዝቦች ሀገር ነበረች፤ የታላላቅ ባህሎች እና የአስደናቂ ቅርሶች ሀገር ነበረች። ጥያቄው “ዛሬስ” የሚለው ነው። ዛሬ በድህነት፣ በኋላ ቀርነትና በረሃብ የምንሰቃይ ከሆነ፣ ታሪካችንን አልዋጀነውም ማለት ነው። ትናንትን የሚዋጀው ዛሬ ነውና። ትናንት የሚቃኘውና የሚተረጎመው በዛሬ መንፈስ ነው። የዛሬ ከፍታ ትናንትን ጨምሮ ከፍ ያደርገዋል። የዛሬ ተዋርዶ ደግሞ ትናንትን ጨምሮ ያወርደዋል። የሀገራችንን ታላቅነት የሚገነዘብ ትውልድ አሁን ተፈጥሯል፡፡ ትውልዱ የድህነትን በትር ደጋግሞ ቀምሷል፤ የኋላቀርነትን አስቀያሚ መልክ እስኪበቃው አይቷል፡፡ የትናንት ስሕተት ያስከተለውን ፍዳ ትከሻው እስኪጎብጥ ለመሸከም ተገድዷል፡፡ የመልክአ ምድር እሥረኝነት ዓይን አፍጥጦ፣ ጥርስ አግጥጦ ሲመጣ የታዘበ ትውልድ ነው፡፡ የችግሩን ልክ መዝኖ መረዳት ብቻ ሳይሆን የመሻገሪያ መርከቡን መገንባት የሚያውቅ ትውልድ ነው፡፡ የትናንት ኩስመናን በዛሬ ትጋት እንደሚያሸንፉ የሚያምኑ ዜጎች ቁጥራቸው በጨመረ ቁጥር የነገ ቁመናችን እንደሚሻሻል ጥርጥር የለውም፡፡ የነቢያት ጽድቅና ትንቢት የቀጠለው የነቢያት አምላክ ክርስቶስ ትንቢታቸውን ፈጽሞ ስለተወለደ ነው። የትንቢት መጻሕፍት ዋጋ ያገኙት በወንጌል መጻሕፍት የተነሣ ነው። ብሉይ ኪዳን ጥቅም ያገኘው በሐዲስ ኪዳን ምክንያት ነው። ሁሉንም ትናንቶች የዋጃቸው ዛሬ ነው። ትናንታችን ዋጋ እና ክብር እንዲኖረው ከፈለግን ዛሬ ተግተን እንሥራ። ብዙ ጊዜያችንን በትናንት ትዝታ እና ትውስታ ውስጥ ከምናሳልፍ፣ በዛሬ ትግልና ውጣ ውረድ ላይ እናጥፋ። ዛሬያችን የተስተካከለና የተቃና ከሆነ፣ ያለ ጥርጥር ትናንትናችን ተገቢውን ክብር ያገኛል። ክርስቶስ ባይወለድ ኖሮ ከክርስቶስ ልደት በኋላ ያለው ዘመን አዲስ ዘመን አይሆንም ነበር። “ነገን ለመተንበይ የተሻለው መንገድ፣ ነገን ራሱን መፍጠር ነው” ይባላል። የሰው ልጆችን ነገ ክርስቶስ ጀመረው፤ ክርስቲያኖች ደግሞ ተራመዱበት። ዛሬ የተሻለ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ነገን የተሻለ አድርገው ይፈጥሩታል። ዛሬን በዋዛና በፈዛዛ፣ በክፋትና በሤራ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ ነገን የባሰ አድርገው ያበላሹታል። የኢትዮጵያ ነገ በዛሬ ሥራና ተጋድሎ እንጂ በዛሬ ምኞትና መሻት ብቻ አይመጣም። አንዳንዶች የኢትዮጵያን ነገ ለማበላሸት ዛሬ በክፋት ሥራዎች ተነክረዋል። እኛ ግን የኢትዮጵያን ነገ ለማቅናት ስንል ነገን በሚዋጁ ሥራዎች ተጠምደናል። ነገን የሚዋጀው ዛሬ መሆኑን ስለምናውቅ፣ ነገን ተቀምጠን አንጠብቀውም። ሠርተን እንደርስበታለን እንጂ። ከቤተልሔም በረት እስከ ቀራንዮ ዐደባባይ የሰው ልጆች ትናንት ሲቀደስ፣ የሰው ልጆች ነገ ሲሠራ መልከ ብዙ ምላሽ ነበረው። የተኙ ነበሩ። የናቁ ነበሩ። ገዳዮች ነበሩ። አሳዳጆች ነበሩ። ሤረኞች ነበሩ። ወሬኞች ነበሩ። አደናቃፊዎች ነበሩ። ነቃፊዎች ነበሩ። በሌላ በኩል ደግሞ ገብቷቸው የተከተሉ፤ ነገን ለመሥራት የተባበሩ፤ እውነት ለመንገር የደፈሩ፤ ለእውነት ለመሠዋት የቆረጡ፤ ጥቂቶች ቢሆኑም ብዙዎችን ለማፍራት የሚተጉ - ነበሩ። የኢትዮጵያ ነገ ሲሠራም ምላሹ ልዩ ልዩ ነው። የሚያሸንፉት ግን ተግተው የሚሠሩት ናቸው። ቪክቶር ሁጎ “ጊዜው የደረሰን ሐሳብ ለማስቆም የሚችል ኃይል በዓለም ላይ የለም” ብሎ ነበር። የኢትዮጵያ ብልጽግና ጊዜው የደረሰ ሐሳብ ነው። ማንም ሊያስቆመው አይቻለውም። የኢትዮጵያ ታላቅነት ጊዜው የደረሰ ሐሳብ ነው። ሊገታው የሚችል ምንም ኃይል የለም። እኛ ዛሬ የቆምነው በትናንት እና በነገ መካከል ነው። ትናንትን በዛሬ ሥራችን ዋጋ እንዲያገኝ እናደርገዋለን። ነገን ደግሞ በዛሬው ሥራችን አሣምረን እንገነባዋለን። የክርስቶስን የልደት በዓል ይሄንን ታሪካዊ ኃላፊነታችንን እያሰብን እናከብረዋለን። በድጋሚ መልካም የልደት በዓል ይሁንልን!! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ታኅሣሥ 28፣ 2018 ዓ.ም Read More |
| የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ተጀመረ ሆሳዕና ፣ ጥር 2፣ 2017 የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ ![]() በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ለኢኮኖሚና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል ብለዋል። ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅምና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ |
| የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ለገና በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ለገና በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፦
በየአካባቢያችን የተጀመሩ የብልፅግና ጉዞ ማሳለጫ ጥረቶችን በአዲስ እሳቤና ብሩህ ተስፋ ማስቀጠል ፣ባህል እንዲሆኑ መስራት፣ሰላምን ማረጋገጥና ማጽናት ተገቢ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል።የዘንድሮውን የገና በዓል በአብሮነትና በመረዳዳት፣በፍቅር፣ በመተጋገዝ፣ በመተሳሰብና ብሩህ ተስፋን ተጎናጽፈን እናክብረው።በዓሉን ስናከብር በሰው ተኮር እሳቤ የተቸገሩትን በማገዝ፣ የታረዙትን በማልበስ፣አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ጧሪ የሌላቸው ወገኖችንና ህጻናትን በመደገፍና በመንከባከብ ማዕዳችንን በማጋራት ልናከብር ይገባል።በዓሉ በሁሉም መስክ ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ፣ቱሩፋቶችና ወረቶች ወደ ባህልና ወደዘላቂ ተግባራት የምንቀይርበት፣በክልሉ የተገኙ ስኬቶችን ለማላቅና የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ተስፋ የምንሰንቅበት ይሆን ዘንድ እመኛለሁ።በአጠቃላይም ለክልላችንና ለአገራችን ህዝቦች በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!ለፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች በድጋሚ መልካም የገና በዓል!! Read More |
| ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ተምሳሌት የሆኑ ናቸው ብለዋል። እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ያላቸውን ሁሉ ለአገራቸው በመስጠት አገልግለዋል። በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል። ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ተመኝተዋል። Read More |



በቅድሚያ ለክልላችንና ለአገራችን የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል/ገና/ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!! በዓሉ የደስታ፣ የሰላም፣ የጤና፣የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንልን! እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ትላልቅ አውደ ዓመቶች አንዱና ትልቁ የገና በዓል ነው። በዓሉ ከሀይማኖታዊ ክንዋኔው ባለፈ የተለያዩ ባህላዊ መስተጋብሮች የሚከወንበት ፣አብሮነትና መተጋገዝ ፣ሰላምና ፍቅር ፣ደስታና ብሩህ ተስፋ በጥምረት የሚንጸባረቁበት ነው።በተለይም በዕለቱ በተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች የሚያደርጓቸው የገና ጨዋታዎች ፣አብሮ መብላት፣መጠያየቅ፣ፍቅርና ደስታው የበዓሉ አይረሴዎች ናቸው።በዓሉን ስናከብር በክልሉ የተጀመረውን ሁሉ አቀፍ የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል ቃላችንን የምናድስበት፣በአፈጻጸም ያገኘናቸውን ስኬቶች ለማላቅና ያጋጠሙ ጉድለቶችን በጋራ ለማረም ቃል የምንገባበት መሆን ይኖርበታል። በክልላችንና በአገራችን የፈነጠቀው የብልፅግና ብሩህ ተስፋ ቀጣይ እንዲሆን፣የተጀመረው ድህነትን ከመሰረቱ የመናድ ራዕይ እንዲሰምር፣የህዝባችንን ዘላቂ ተጠቃሚነትና ክብር የማረጋገጥ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ያስፈልጋል።
የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ