የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል
እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ!
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለዘንድሮዉ የገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ ! አደረሰን! እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በታላላቅ ሀገራዊ ስኬቶች ታጅባ፣ የማንሰራራት ዘመን ጉዞዋን እያጠናከረች በምትገኝበት ምዕራፍ ላይ የምናከብረዉ የዘንድሮዉ የገና በዓል ፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴቶቻችንን በማጠናከር ፣በመደመር እሳቤ ተሳስረን፣ ለአዳዲስ ሀገራዊ ብስራቶች ፣በጋራ ለመትጋት መነሳሳትን የምንፈጥርበት ነዉ።
የገና በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነዉ።
የገና በዓል ከሃይማኖታዊ ትዉፊቶቹ እና አስተምህሮቶቹ ባሻገር ፣ የመልካም ምኞት መግለጫ ስጦታዎችን በመለዋወጥ ፣ ፍቅርንና ትብብርን ለማደስ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነዉ።
በዓሉ ማህበራዊ እሴቶችን የሚያነቃቃ፣ የወንድማማችነት/የእህትማማችነት መንፈስን የሚያድስና በአዲስ መንፈስ ለአዲስ ስኬት መነሳሳትን የሚያጎናጽፍ ነዉ።
በዓሉን ስናከብር ብሩህ ተስፋንና አሻጋሪ ህልምን ሰንቀን ፣ የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴቶችን አልቀን ፣ ለጋራ ሠላምና ዕድገት በጋራ ለመትጋት ዝግጁነታችንን ከፍ በማድረግ መሆን ይኖርበታል።
መልካም የገና በዓል !
አመሠግናለሁ !
